የማኅበራዊ ሚዲያ መርሆዎች እና ደንቦች

 1. ኮማሪ ቢቨሬጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹን፤አካውንቶቹን፤ድህረ ገጾቹን እና መተግበሪያዎቹን( ከዚህ በኋላ በአንድነት “ገጾች” ተብለው የሚጠቀሱትን) በአግባቡ እና በተገቢው መንገድ ለመጠቀም ሲባል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማህበራዊ ሚዲያ ደንቦቹን እዚህ አስፍሯል። ይህንን ድንብ እና ሁኔታ ሲቀበሉ ደንቦቹን በአግባቡ የተረዱ እና ገጾቹንም ለመጠቀም በቁ መሆንዎን ያረጋግጣሉ።
 2. የሕግ ገደቦች፤  እኛ የአልኮል ምርቶችን የምናመርት ነን። ምርቶቻቸንን እና ገጾቻቸንን ለመጠቀም  ቢያንስ ከ21ዓመት በላይ እድሜ ሊሆናችሁ ይገባል። ማናቸውም አይነት ከ21ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች የሚፈጸም ገጾቻችን መጠቀም  ያልተፈቀደ፤ ያልተገባ እና ይህንን ደንብ የሚጥስ ነው። የእኛን ገጾች ሲጠቀሙ እድሜዎት 21 እና ከዚያ በላይ መሆኑን እያረጋገጡ ነው።
 3. ከጊዜ ወደ ጊዜ በገጾቻችን ላይ ጥሩ እና ደስ ይላሉ የምንላቸውን ነገሮች እናጋራልን። አልፎ አልፎ ደግሞ የሌሎችን ተጠቃሚዎች ፖስት ወይም ትዊት ልናጋራ እንችላለን ወይም በእኛ ፖስት ላይ ሶስተኛ ወገኖችን ልንጠቅስ እንችላለን። ይህ ማለት ግን እኛ ያጣቀስናቸው ገጾች፤ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች እና ምርቶች ትክክለኛነት ማረጋገጫ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም።
 4. በእኛ ገጾች ላይ በእኛ ወይም በሶስተኛ ወገን ለሚለጠፉ ፖስቶች ትክክለኛንትን ማረጋገጥ አንችልም። በሌሎች የሚደረጉ ፖስቶችን በማናቸውም አይነት መልኩ ቢሆን ስለትክክለኛነታቸው አናረጋግጥም ሃላፊነትም አንወስድም። በእኛ ገጾች ላይ በሶስተኛ ወገኖች ለሚደረጉ ፖስቶች በህግ እኛ ተጠያቂ አይደለንም። በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚያያዙ ሊንኮችን ትክክለኛነት እኛ አናረጋግጥም። እነዚህ ሊንኮች ኮምፒዩተሮን ወይም ሌላ የመገልገያ ቀሶች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ወይም ወዳልተፈለገ ገጽ ሊወስዶት ይችላል። 
 5.  በመንግስት አካል ስንጠየቅ ገጾቻችን ላይ ከርስዎ ጋር የነበረንን ንግግር እና የርስዎን የእኛ ገጽ ላይ የነበሮትን እንቅስቃሴ ልናሳውቅ እንችላለን።
 6. እርስዎ በእኛ ገጾች ላይ ለሚለጥፏቸው ፖስቶች ወይም ስለሚያጋሯቸው ሊንኮች በተመለከተ እዚህ በተዘረዘሩት የማህበራዊ ሚዲያ ደንቦቻችን ለመገዛት ተስማምተዋል። በተጨማሪም የእርስዎን ፖስቶች ለማስተካከል ወይም ለማጥፋት ሙሉ ስልጣን ያለን ስለመሆኑ ያረጋግጣሉ። በተጨማሪም የርስዎ ፖስቶች ወይም አስተያየቶች አግባብነት ያላቸውን ሕጎችን ወይም ደንቦችን የተከተሉ እና ያከበሩ መሆኑን እና እርስዎ ከኮማሪ ጋር የገቡትን ሌሎች ግዴታዎች ጭምረ ያከበረ ስለመሆኑ ያረጋግጣሉ። በማናቸውም የማህበራዊ ገጻችን ላይ የሚጽፏቸው አስተያየቶች፤ የሚለጥፏቸው ፖስቶች ወይም የሚያጋሯቸው ሊንኮች በተመለከተ ለኮማሪ በድጋሚ ወይም አስተካክሎ እንዲለጥፋቸው፤ እንዲያሳትማቸው፤ እንዲያስተካክላቸው ወይም ከእነሱ ላይ ተነስቶ ሌሎች የፈጠራ ስራዎችን እንዲሰራ እና በማናቸውም ሚዲያ ወይም ለማናቸውም አይነት አላማ እንዲጠቀምበት የማይሻር መብት መስጠትዎን ያረጋግጣሉ።
 7. ማናቸውም አይነት በእኛ ገጽ ላይ የሚያደርጓቸው የድምጽ፤ የምስል ወይም የጽሁፍ እንቅስቃሴዎች ይህን የማህበራዊ ሚዲያ ደንብ የተከተለ መሆን አለበት። ማናቸውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማያሟላ ወይም ኮማሪ አግባብ አይደለም ብሎ ያመነበትን ፖስቶች ከገጹ ላይ ማስወገድ ይችላል።

የእርስዎ አስተያየት የሚከተሉትን የያዘ እንዲሆን ይጠበቃል። 

 • ፍሬ ነገሮችን የተመለከተ ሲሆን ትክክለኛ፤
 • አስተያየቶችን የተመለከተ ሲሆን በቅንነት የተሰጠ፤
 • ክብር ያለው፤ እና
 • የኢትዮጲያን ወይም ሌላ የሚለጥፈበትን ሀገር ህግ ያከበረ መሆን ይገባዋል።

የእርስዎ አስተያየት የሚከተሉትን መያዝ የለበትም።

 • ህገወጥ የሆኑ ጥላቻን፤ጥቃትን፤ አስነዋሪነትን ወይም ጸብ ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች የያዙ፤
 • ወሲብ ቀስቃሽ የሆኑ ይዘቶች፤
 • ሌሎችን የሚጎዳ ወይም እንዲጎዱ የሚያነሳሳ ይዘት፤
 • ለመጠጥ እድሚያቸው ያልደረሱ ሰዎችን አላማ ያደረጉ ይዘቶች፤
 • እድሚያቸው ያልደረሱ ሰዎችን እንዲጠጡ፤ ጠጥቶ ማሽከርከርን ወይም ከመጠን በላይ አልኮል መጠቀምን የሚያበረታቱ፤የሚያሰተወወቁ ወይም የሚያደንቁ ይዘቶች፤
 • ጸብን የሚያበረታቱ፤
 • ሌሎች ላይ በዘራቸው፣ በሀይማናቶቸው፣በጾታቸው፣ በሀገራቸው፣በአካል ጉዳተኝነታቸው ወይም እድሜቸው ምክንያት ጥቃት እንዲደርስባቸው የሚያበረታቱ ይዘቶች፤
 • የሌሎችን የኮፒራይት መብት፤ የንግድ ምልክት ወይም ማናቸውም አይነት የአዕምሯዊ ንብረት መብት ላይ ጥሰትን የሚፈጽሙ ይዘቶች፤
 • ማናቸውም ሰውን የሚያሳስቱ ይዘቶች፤
 • ህገወጥነትን እና ኢሞራል የሆኑ እንቅስቃሴዎችን የሚያበራታቱ ይዘቶች፤
 • አስፈራሪ የሆኑ፤ ወይም ያለግባብ የሌላን ሰው ግላዊ ህይወት የሚረብሹ ይዘቶች፤
 • ማናቸውንም ሰው የሚያዋርዱ፣ የሚያበሳጩ፤ የሚያስፈራሩ ወይም የሚያጠቁ
 • ሌላን ሰው በመምሰል የሚሰጡ ወይም ከሌላ ሰው ጋር ያለን ግንኙነት ወይም የራስን ማንነት በመደበቅ የሚሰጡ ይዘቶች፤
 • ከእኛ ሳይሰጥዎ የርስዎን አስተያየት ከእኛ እንደተሰጡ የሚያስመስል ይዘት ያላቸው ልጥፎች፤
 • ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን በተለይም የአእምሯዊ ንብረት ውጤት የሆኑትን የኮፒ ራይት መብት እና ንግድ ምልክት ጥሰትን እንዲፈጸም የሚያደርጉ፤ የሚያበረታቱ ወይም የሚረዱ ልጥፎችን
 • የሌላ ግለሰብን የግል መለያ የሆኑትን እንደ ስልክ ቁጥር ወይም ሌላ መሰል አካባቢያዊ አድራሻ የመሳሰሉትን በቀላሉ ማንነትን መለያ የሆኑ ነገሮችን መለጠፍ  
 • ስለሌሎች የመጠጥ ምርት እና ምልክቶች መጥፎ ወይም አሉታዊ ነገርን የያዙ ልጥፎች
 • ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ወይም ፖለቲካዊ እንድምታ መፍጠርን አላማ ያደረጉ ልጥፎች

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት እንደ ምሳሌ የሚያገለግሉ እንጂ እነዚሁ ብቻ አለመሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል።

 • ኮፒ ራይት / የመጠቀም መብት

በገልጽ በተቃራኒ ካልተገለጽ በስተቀር በገጾቻችን ላይ የሚለጠፉ ወይም የሚገኙ ሁሉ የአእምሯዊ ንበረት መብትነታቸው በኮማሪ የተያዘ ወይም ሌሎች ኮማሪ እንዲጠቀምበት በፈቀዱ ሰዎች የተያዘ እና የተጠበቀ ነው።

በኮማሪ ገጾች ላይ የሚለጠፉ ይዘቶችን በጊዚያዊነት እንዲያወርዱ እና ለግል እና ለንግድ ላልሆነ አላማ እንዲጠቀሙበት እንፈቅዳለን። ይህ ፈቃድ እንጂ መብትን ማስተላለፍ አይደለም፤ ስለሆነም የሚከተሉትን እንዳያደርጉ እናሳስባለን።

 • በግልጽ ካላመለከተ በስተቀር ይዘቱ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ኮፒ ማድረግ፤
 • ይዘቱን ለንግድ አላማ ማዋል፤ ወይም
 • በ ተቆጣጣሪ ባለስለልጣናት እንዲለጠፉ የተደረጉ አስገዳጅ ምልክቶችን ማሰወገድ ወይም ማንሳት
 • ኮማሪ በገጾቹ ላይ ወይም ተያያዥ በሆኑ የሶስተኛ ወገን ገጾች ላይ ስለሚለጠፉ እቃዎች አጠቃቀምን በተመለከተ ስለትክክለኛነታቸው ወይም አስተማማኝነታቸው ማረጋገጫ እና ዋስትና አይሰጥም። ገጾቻችን ከስህተት ወይም ከቫይረስ የጸዱ ስለመሆናቸውም ወይም ገጾች ላይ የሚያጋጥም ስህተትን ማስተካከልን በተመለከተ ኮማሪ ዋስትና እና ማረጋገጫ አይሰጥም። በገጾቻቸን ላይ ያሉት ይዘቶች ፎቶዎች፤ ጽሁፎች ወይም ግራፊክሶችን ጨምሮ መረጃን ለመስጠት አላማ ብቻ የተደረጉ እንጂ እንደ ሽያጭ ስምምነት ወይም ግዢን ማረጋገጫ ተደርገው መቆጠር የለባቸውም።
 • ኮማሪ በተጠቃሚዎች ወይም ገጾቻችንን እንዲያስተዳድሩ ባልተፈቀደላቸው ሰራተኞቹ ወይም ወኪሎች አማካኝነት በገጹ ላይ ለሚለጠፉ ይዘቶች  ሀላፊነት አይወስድም። በሌሎች የሚለጠፉ ይዘቶች በኮማሪ የተሻሻሉ ወይም የኮማሪን ሀሳብ የሚያንጸባርቁ ተደርገው መወሰድ የለባቸውም።
 • ገጾቻችንን የሚጠቀሙት በራስዎ ሃላፊነት ነው። በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ኮማሪ ወይም አጋሮቹ ገጾችን በመጠቀማችሁ የተነሳ ወይም ገጾችን በተመለከተ ወይም ገጾቹን ለመጠቀም ባለመቻላችሁ ምክንያት ለሚደርስባችሁ ቀጥተኛ ሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ፤ ድንገተኛ ወይም ቅጣትን ወይም የገንዘብ ኪሳራን የሚያመጣ ጉዳቶችን ወይም ቅጣቶችን በተመለከተ ሀላፊነትን አይወስድም።  ይህ ሀላፊነትን አለመውሰድ ስለጉዳዩ ለኮማሪ በቃል ወይም በጽሁፍ እንዲያውቀው ቢደረግም ቀሪ የሚሆን አይደለም። በገጾቻችን ድስተኛ አለመሆንዎ ሊሰጥዎት የሚችለው ብቸኛ መፍትሄ ገጻችንን መጠቀም ማቆም ብቻ ነው። ይህንን ድንብ ባላማክበርዎ ወይም ተያያዥ መመሪያዎችን ባለማክበርዎ ወይም ማናቸውም ገጾቻችንን የተመለከተ ከሶፍትዌር ጋር የተያያዘ ወይም ቴክኒካል ወይም ሰውሰራሽ ስህተቶችን በተመለከተ ለሚመጡ ኪሳራዎች ወይም ጉዳቶች ሃላፊነትን አንወስድም።
 •  ለርስዎ ማሳወቅ ሳይጠበቅብን በማናቸውም ጊዜ ገጻችን ላይ የሚገኙትን ይዘቶች፣ የገጾቻችንን ባህሪዎች ወይም ተፈጻሚነት ልናሻሽል ወይም ሙሉ በሙሉ ልናጠፋው እና ልናቋርጥ መብት አለን።
 • ኮማሪ በማናቸውም ጊዜ የርስዎን የገጻችንን ተጠቃሚነት ሊያቋርጥ ይችላል። በተጨማሪም ኮማሪ ገጾቹን ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የመቀየር፤ የማገድ ወይም የማቋረጥ ሙሉ መብቱን እንደተጠበቁ ናቸው።
 • እነዚህ ደንቦች በኢትዮጲያ ህጎች መሰረት የጽኑ እና የሚተረጎሙ ይሆናሉ። እንዲሁም እርስዎ ይህንን ደንብ ወይም ከዚሁ ጋር ተያያዠ የሆኑ አለመስማማቶችን በተመለከተ ለሚነሱ ማናቸውም አይነት ክርክሮች በአዲስ አበባ የሚገኙ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በብቸኝነት እንዲዳኙን የማይቀየር ፈቃዶትን ስለመስጠትዎ ያረጋግጣሉ።

የማህበራዊ ድረገጾቻችንን በተመለከተ ለሚኖሮት ጥያቄዎች ወይም ለበለጠ መረጃ በኢሜይል አድራሻችን  inquiry@komari.com መልክት ቢልኩልን ወይም በ6962 ቢደውሉልን እርስዎን ለመርዳት ድስተኞች ነን።